የDrive አርማ

ሁሉም የእርስዎ ፋይሎች፣ እርስዎ ሲዘጋጁ እነሱም ዝግጁ የሚሆኑ

ወደ Google Drive ይሂዱ
የDrive ፋይል አይነቶች አዶዎች

ማንኛውም አይነት ፋይል ያከማቹ

Drive በነጻ የ15 ጊባ የGoogle መስመር ላይ ማከማቻ ያስጀምረዎታል፤ በዚህም ፎቶዎችን፣ ታሪኮችን፣ ንድፎችን፣ ስዕሎችን፣ ቀረጻዎችን፣ ቪዲዮዎችን – ማንኛውም ነገር ማስቀመጥ ይችላሉ።

በGoogle Drive ላይ ያሉ ፋይሎች በበርካታ መሣሪያዎች ላይ ይታያሉ

የእርስዎን ነገሮች ሁሉም ቦታ ይመልከቷቸው

በDrive ውስጥ ያሉ የእርስዎ ፋይሎች ከማንኛውም ዘመናዊ ስልክ፣ ጡባዊ ወይም ኮምፒውተር ሊደረስባቸው ይችላሉ። ስለዚህ የትም ቦታ ቢሄዱ ፋይሎችዎ ተከትለው ይመጣሉ።

ፋይሎች Drive ላይ ለጓደኛዎችዎ ያጋሩ

ፋይሎችን እና አቃፊዎችን ያጋሩ

ሌሎች ሰዎች የሚፈልጓቸውን ፋይሎች እንዲመለከቱ፣ እንዲያወርዱ እና እንዲተባበሩባቸው በፍጥነት መጋበዝ ይችላሉ–ምንም የኢሜይል አባሪ አያስፈልግም።